ሳምንት 10 · ቀን 50 (አርብ)
📅 Hidar 11, 2019
ኦሪት ዘኍልቍ 22, 23, 24, 25 · የሉቃስ ወንጌል 1
ኦሪት ዘኍልቍ
ምዕራፍ 22
ባላቅ በለዓምን አስጠራ
1.ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ ሞዓብ ሜዳ ተጕዘው ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ከኢያሪኮ ማዶ ሰፈሩ። 2.በዚህ ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እስራኤል በአሞራውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፤ 3.ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ተሸበረ፤ በርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሀት ተውጦ ነበር። 4.ሞዓባውያንም የምድያምን ሽማግሌዎች፣ “በሬ የመስክ ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ፣ ይህም ሰራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሏቸው።ስለዚህ በዚያ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ የነበረው የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ 5.ከወንዙ ዳር ባለች በትውልድ አገሩ በምትገኝ በፐቶር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞች ላከ፤ እንዲህም አለ፤
“እነሆ፤ ከብዛቱ የተነሣ ምድሩን የሸፈነ ሕዝብ ከግብጽ ወጥቶ በአቅራቢያዬ ሰፍሯል። 6.ስለዚህ ይህን ሕዝብ መቋቋም ስለማልችል መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባትም ድል አድርጌ ከአገሪቱ ላስወጣቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል፤ አንተ የምትባርከው ቡሩክ፣ የምትረግመውም ርጉም እንደሚሆን ዐውቃለሁና።” 7.የሞዓብና የምድያም ሽማግሌዎችም ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ሄዱ፤ በለዓም ዘንድ በደረሱ ጊዜም የባላቅን መልእክት ነገሩት። 8.በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚሰጠኝን መልስ አመጣላችኋለሁና የዛሬን ሌሊት እዚሁ ዕደሩ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ አለቆች ከርሱ ዘንድ ቈዩ። 9.እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፣ “ከአንተ ጋራ ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። 10.በለዓምም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “የሞዓብ ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ይህን መልእክት ልኮብኛል፤ 11.‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድሩን ገጽ አጥለቅልቆታል፤ ስለዚህ መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባት ልዋጋቸውና ላባርራቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል።’ ” 12.እግዚአብሔር ግን በለዓምን፣ “ዐብረሃቸው አትሂድ፤ የተባረከ ሕዝብ ስለ ሆነም አትርገመው” አለው። 13.በማግስቱም ጧት በለዓም ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፣ “ዐብሬአችሁ እንዳልሄድ እግዚአብሔር ከልክሎኛልና እናንተ ወደ አገራችሁ ተመለሱ አላቸው።” 14.ስለዚህ የሞዓብ አለቆች ወደ ባላቅ ተመልሰው፣ “በለዓም ዐብሮን ለመምጣት እንቢ አለን” አሉት። 15.ከዚያም ባላቅ ከፊተኞቹ ይልቅ ቍጥራቸው የበዛና ይበልጥ የተከበሩ ሌሎች አለቆች ላከ። 16.እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፤
“የሴፎር ልጅ ባላቅ ይህን እንድንነግርህ ልኮናል፤ ወደ እኔ ለመምጣት የሚያግድህ ምንም ነገር አይኑር፤ 17.ወሮታህን በእጅጉ እከፍላለሁ፤ የምትለውንም ሁሉ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ መጥተህ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።” 18.በለዓም ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣስ ከዚያ ያለፈ ወይም ያነሰ ማንኛውንም ነገር ማድረግ አልችልም። 19.አሁንም ሌሎቹ እንዳደረጉት ሁሉ፣ እናንተም ዛሬ እዚሁ ዕደሩና እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ደግሞ ልወቅ።” 20.በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ፣ “እነዚህ ሰዎች የመጡት እንድትሄድላቸው እስከ ሆነ ድረስ ዐብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ።”
የበለዓም አህያ
21.በለዓም በጧት ተነሣ፤ አህያውንም ጭኖ ከሞዓብ አለቆች ጋራ ሄደ። 22.ይሁን እንጂ በለዓም በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር በጣም ተቈጥቶ ስለ ነበር የእግዚአብሔር መልአክ ሊቃወመው በመንገዱ ላይ ቆመ። በለዓምም በአህያው ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ሁለት አሽከሮቹም ዐብረው ነበሩ። 23.አህያዪቱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ በመንገድ ላይ መቆሙን ባየች ጊዜ ከመንገድ ወጥታ ዕርሻ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገዱ እንድትመለስ መታት። 24.ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በሁለቱም በኩል ግንብ ባለበት በሁለት የወይን ተክል ቦታ መካከል በሚገኝ ጠባብ መተላለፊያ ላይ ቆመ። 25.አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ ባየች ጊዜ ወደ ግንቡ ተጠግታ የበለዓምን እግር አጣበቀችው፤ ስለዚህም እንደ ገና መታት። 26.የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ፊት ሄድ ብሎ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ መተላለፊያ በሌለበት ጠባብ ቦታ ላይ ቆመ። 27.አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ ባየች ጊዜ ከበለዓም በታች ተኛች፤ በለዓም ተቈጥቶ ነበርና በበትሩ ደበደባት። 28.ከዚያም እግዚአብሔር የአህያዪቱን አፍ ከፈተ፤ በለዓምንም፣ “እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌህ ነው?” አለችው። 29.በለዓምም መልሶ አህያዪቱን፣ “ስላላገጥሽብኝ ነዋ! በእጄ ሰይፍ ይዤ ቢሆን ኖሮ አሁኑኑ በገደልሁሽ ነበር” አላት። 30.አህያዪቱም ደግሞ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “ከብዙ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የተቀመጥህብኝ አህያህ አይደለሁምን? ታዲያ ይህን የመሰለ ነገር የማድረግ ልማድ ነበረኝ?”እርሱም፣ “በጭራሽ!” አላት። 31.በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የበለዓምን ዐይን ከፈተ፤ እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ እንደ ያዘ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ፤ ጐንበስ ብሎም በግንባሩ ተደፋ። 32.የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “አህያህን እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታሃት ስለ ምንድን ነው? መንገድህ በፊቴ ጠማማ ስለ ሆነ ልቃወምህ መጥቻለሁ። 33.አህያዪቱ አይታኝ ሦስቱንም ጊዜ ከፊቴ ዞር ባትልማ ኖሮ በእውነት እስካሁን አንተን በገደልሁህ፣ አህያዪቱን ግን በሕይወት በተውኋት ነበር።” 34.በለዓምም የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ እኔን ለመቃወም መንገዱ ላይ መቆምህን አላወቅሁም፤ አሁንም ደስ የማትሰኝ ከሆነ እመለሳለሁ” አለው። 35.የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፣ “መሄዱን ከሰዎቹ ጋራ ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው። ስለዚህ በለዓም ከባላቅ አለቆች ጋራ ሄደ። 36.በለዓም በመምጣት ላይ መሆኑን ባላቅ በሰማ ጊዜ በግዛቱ ዳርቻ በአርኖን ወሰን ላይ ወደምትገኘው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊቀበለው ወጣ። 37.ባላቅ በለዓምን፣ “በቶሎ እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረምን? ለምን አልመጣህም? በርግጥ ወሮታህን ልከፍል የማልችል ሆኜ ነውን?” አለው። 38.በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት። 39.ከዚያም በለዓም ከባላቅ ጋራ ወደ ቂርያት ሐጾት ሄደ። 40.ባላቅም ከብቶችና በጎች ሠዋ፤ ከፊሉንም ለበለዓምና ከርሱ ጋራ ለነበሩት አለቆች ሰጣቸው። 41.በማግስቱም ጧት ባላቅ በለዓምን ወደ ባሞትባኣል አወጣው፤ እዚያም ሆኖ ሕዝቡን በከፊል አየ።
ምዕራፍ 23
የመጀመሪያው የበለዓም ንግር
1.በለዓም፣ “እዚህ ሰባት መሠዊያ ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት አውራ በጎችም አዘጋጅልኝ” አለው። 2.ባላቅም በለዓም እንደ ነገረው አደረገ፤ ሁለቱም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ አቀረቡ። 3.ከዚያም በለዓም ባላቅን፣ “እኔ ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው። ከዚያም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኰረብታ ሄደ። 4.እግዚአብሔር ተገናኘው፤ በለዓምም፣ “እነሆ፤ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ በእያንዳንዱም ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ አቅርቤአለሁ” አለው። 5.እግዚአብሔርም በበለዓም አፍ መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመልሰህ ይህን መልእክት ንገረው” አለው። 6.እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው። 7.ከዚያም በለዓም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“ባላቅ ከአራም አመጣኝ፣
የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች።
‘ና ያዕቆብን ርገምልኝ፤
መጥተህም እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ። 8.እግዚአብሔር ያልረገመውን፣
እኔ እንዴት ረግማለሁ?
እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ፣
እንዴት አወግዛለሁ? 9.ከዐለታማ ተራሮች ጫፍ ሆኜ አየዋለሁ፤
በከፍታዎቹም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤
ተለይቶ የሚኖረውን፣
ራሱንም ከሌሎች ሕዝቦች ጋራ የማይቈጥረውን ሕዝብ አያለሁ። 10.የያዕቆብን ትቢያ ማን ቈጥሮ ይዘልቃል?
የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቈጥረዋል።
የጻድቁን ሞት እኔ ልሙት፤
ፍጻሜዬም የርሱ ዐይነት ፍጻሜ ትሁን!” 11.ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው። 12.እርሱም መልሶ “እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን መናገር አይገባኝምን?” አለው።
ሁለተኛው የበለዓም ንግር
13.ከዚህ በኋላ ባላቅ፣ “እነርሱን ማየት ወደምትችልበት ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ በእዚያም ሁሉን ሳይሆን በከፊል ብቻ ታያቸዋለህ፤ እዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው። 14.ስለዚህም በፈስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወዳለው ወደ ጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያ ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ። 15.በለዓምም ባላቅን፣ “እርሱን ለመገናኘት ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ” አለው። 16.እግዚአብሔር በለዓምን ተገናኘው፤ በአፉም መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና ይህን መልእክት ንገረው” አለው። 17.እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ ባላቅም፣ “እግዚአብሔር ምን አለ?” ሲል ጠየቀው። 18.ከዚያም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“ባላቅ ሆይ ተነሣ፤ ስማኝ፤
የሴፎር ልጅ ሆይ አድምጠኝ፤ 19.ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤
ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤
ተናግሮ አያደርገውምን?
ተስፋ ሰጥቶስ አይፈጽመውምን? 20.እባርክ ዘንድ ትእዛዝ ተቀብያለሁ፤
እርሱ ባርኳል፤ እኔም ልለውጠው አልችልም። 21.“በያዕቆብ መጥፎ ነገር አልተገኘም፤
በእስራኤልም ጕስቍልና አልታየም፤
እግዚአብሔር አምላኩ ከርሱ ጋራ ነው፤
የንጉሡም እልልታ በመካከላቸው ነው። 22.እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤
ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው። 23.በያዕቆብ ላይ የሚሠራ አስማት የለም፤
በእስራኤልም ላይ የሚሠራ ሟርት አይኖርም፤
ለያዕቆብና ለእስራኤል፣
‘እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ!’ ይባልላቸዋል። 24.ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤
ያደነውን እስኪያነክት፣
የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣
እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።” 25.በዚህ ጊዜ ባላቅ በለዓምን፣ “እንግዲያውስ ፈጽሞ አትርገማቸው፤ ፈጽሞም አትመርቃቸው!” አለው። 26.በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚለኝን ሁሉ ማድረግ እንዳለብኝ አልነገርሁህምን?” ሲል መለሰለት።
ሦስተኛው የበለዓም ንግር
27.ከዚህ በኋላ ባላቅ በለዓምን፣ “በል እንግዲያው ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ፤ ከዚያ ሆነህ እንድትረግምልኝ ምናልባት እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው። 28.ባላቅም በለዓምን ምድረ በዳው ቍልቍል ወደሚታይበት ወደ ፌጎር ጫፍ አወጣው። 29.በለዓምም፣ “ሰባት መሠዊያዎች እዚህ ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት አውራ በጎችም አዘጋጅልኝ” አለው። 30.ባላቅም በለዓም እንደ ነገረው አደረገ፤ በእያንዳንዱም መሠዊያ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።ምዕራፍ 24
1.በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን መባረክ እንደ ወደደ ባየ ጊዜ፣ እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ አስማት ለመሻት አልሄደም፤ ነገር ግን ፊቱን ወደ ምድረ በዳ መለሰ።
2.በለዓም አሻግሮ ተመልክቶ እስራኤል በየነገድ በየነገዱ ሆኖ መስፈሩን ሲያይ የእግዚአብሔር መንፈስ በላዩ መጣበት፤
3.ንግሩንም እንዲህ ሲል ጀመረ፤
“የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት፣
የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፣ 4.የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣
ሁሉን ቻይ የአምላክን ራእይ የሚያይ፣
ከመሬት የተደፋው ዐይኖቹም የተከፈቱለት ሰው ንግር፤ 5.“ያዕቆብ ሆይ፤ ድንኳኖችህ፣
እስራኤል ሆይ፤ ማደሪያዎችህ እንዴት ያማሩ ናቸው! 6.“እንደ ሸለቆዎች፣
በወንዝ ዳር እንዳሉም የአትክልት ስፍራዎች ተዘርግተዋል፤
በእግዚአብሔር እንደ ተተከሉ አደሶች፣
በውሃም አጠገብ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው። 7.ከማድጋቸው ውሃ ይፈስሳል፤
ዘራቸውም የተትረፈረፈ ውሃ ያገኛል።
“ንጉሣቸው ከአጋግ ይልቃል፤
መንግሥታቸውም ከፍ ከፍ ይላል። 8.“እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤
ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው፤
ጠላቶች የሆኗቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤
ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤
በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል። 9.እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤
እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው?
“የሚባርኩህ ቡሩክ፣
የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።” 10.ከዚያም ባላቅ፣ በበለዓም ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨብጭቦ እንዲህ አለው፤ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ አንተ ግን ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው። 11.በል ቶሎ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፤ ወሮታህን አሳምሬ ልከፍልህ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እንዳታገኝ ከለከለህ።” 12.በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ወደ እኔ ለላክሃቸው ሰዎች እንዲህ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን? 13.‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር የሚለውን ብቻ ከመናገር በቀር ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’ 14.እንግዲህ ወደ ሕዝቤ እመለሳለሁ፤ ይሁን እንጂ በሚመጣው ዘመን ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።”
“የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፤
የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት ሰው ንግር። 16.የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣
ከልዑልም ዕውቀትን ያገኘው፣
ከሁሉን ቻይ ራእይ የሚገለጥለት፣
መሬት የተደፋው፣ ዐይኖቹም የተገለጡለት ሰው ንግር፤ 17.“አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤
እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤
ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤
በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል።
የሞዓብን ግንባሮች፣
የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቅቃል። 18.ኤዶም ይሸነፋል፤
ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤
እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል። 19.ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤
የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።”
“አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤
በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።” 21.ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤
“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤
ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቷል፤ 22.ያም ሆኖ ግን እናንተ ቄናውያን፤
አሦር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።” 23.ከዚያም ንግሩን ቀጠለ፤
“ወዮ! አምላክ ይህን
ሲያደርግ ማን ይተርፋል? 24.መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤
አሦርንና ዔቦርን ይይዛሉ፤
እነርሱም ደግሞ ይደመሰሳሉ።” 25.ከዚህ በኋላ በለዓም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።
“የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት፣
የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፣ 4.የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣
ሁሉን ቻይ የአምላክን ራእይ የሚያይ፣
ከመሬት የተደፋው ዐይኖቹም የተከፈቱለት ሰው ንግር፤ 5.“ያዕቆብ ሆይ፤ ድንኳኖችህ፣
እስራኤል ሆይ፤ ማደሪያዎችህ እንዴት ያማሩ ናቸው! 6.“እንደ ሸለቆዎች፣
በወንዝ ዳር እንዳሉም የአትክልት ስፍራዎች ተዘርግተዋል፤
በእግዚአብሔር እንደ ተተከሉ አደሶች፣
በውሃም አጠገብ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው። 7.ከማድጋቸው ውሃ ይፈስሳል፤
ዘራቸውም የተትረፈረፈ ውሃ ያገኛል።
“ንጉሣቸው ከአጋግ ይልቃል፤
መንግሥታቸውም ከፍ ከፍ ይላል። 8.“እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤
ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው፤
ጠላቶች የሆኗቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤
ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤
በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል። 9.እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤
እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው?
“የሚባርኩህ ቡሩክ፣
የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።” 10.ከዚያም ባላቅ፣ በበለዓም ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨብጭቦ እንዲህ አለው፤ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ አንተ ግን ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው። 11.በል ቶሎ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፤ ወሮታህን አሳምሬ ልከፍልህ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እንዳታገኝ ከለከለህ።” 12.በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ወደ እኔ ለላክሃቸው ሰዎች እንዲህ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን? 13.‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር የሚለውን ብቻ ከመናገር በቀር ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’ 14.እንግዲህ ወደ ሕዝቤ እመለሳለሁ፤ ይሁን እንጂ በሚመጣው ዘመን ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።”
አራተኛው የበለዓም ንግር
15.ከዚያም እንዲህ ሲል ንግሩን ጀመረ፤“የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፤
የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት ሰው ንግር። 16.የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣
ከልዑልም ዕውቀትን ያገኘው፣
ከሁሉን ቻይ ራእይ የሚገለጥለት፣
መሬት የተደፋው፣ ዐይኖቹም የተገለጡለት ሰው ንግር፤ 17.“አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤
እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤
ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤
በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል።
የሞዓብን ግንባሮች፣
የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቅቃል። 18.ኤዶም ይሸነፋል፤
ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤
እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል። 19.ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤
የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።”
የመጨረሻዎቹ የበለዓም ንግሮች
20.ከዚያም በለዓም አማሌቅን አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤
በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።” 21.ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤
“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤
ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቷል፤ 22.ያም ሆኖ ግን እናንተ ቄናውያን፤
አሦር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።” 23.ከዚያም ንግሩን ቀጠለ፤
“ወዮ! አምላክ ይህን
ሲያደርግ ማን ይተርፋል? 24.መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤
አሦርንና ዔቦርን ይይዛሉ፤
እነርሱም ደግሞ ይደመሰሳሉ።” 25.ከዚህ በኋላ በለዓም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።
ምዕራፍ 25
ሞዓብ እስራኤልን አሳሳተ
1.እስራኤላውያን በሰጢም በነበሩበት ጊዜ ወንዶቹ ከሞዓብ ሴቶች ጋራ ማመንዘር ጀመሩ። 2.እነዚህም ሴቶች ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ሕዝቡን ጋበዙ፤ ሕዝቡም መሥዋዕቱን በላ፤ ለአማልክቱም ሰገደ። 3.ስለዚህ እስራኤል በኣል ፌጎርን በማምለክ ተባበረ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በላዩ ነደደ። 4.እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አስፈሪው የእግዚአብሔር ቍጣ ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ ፀሓይ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ስቀላቸው” አለው። 5.ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፣ “እያንዳንዳችሁ በኣል ፌጎርን በማምለክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።” 6.ከዚህ በኋላ ሙሴና መላው የእስራኤል ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ እያለቀሱ ሳለ፣ አንድ እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተ ሰቡ መጣ። 7.የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ይህን ባየ ጊዜ ማኅበሩን ትቶ ጦሩን በእጁ በመያዝ፣ 8.እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው። ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤ 9.ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺሕ ደርሶ ነበር። 10.እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 11.“የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እኔ ለክብሬ በመካከላቸው እንደምቀና ስለ ቀና ቍጣዬን ከእስራኤላውያን መልሶታል፤ ስለዚህ እኔም በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋኋቸውም፤ 12.ስለዚህ እነሆ እኔ የሰላም ቃል ኪዳኔን ከርሱ ጋራ እንደማደርግ ንገረው። 13.ለአምላኩ ክብር ቀንቶ ለእስራኤላውያን ስላስተሰረየላቸው፣ እርሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል።” 14.ከምድያማዊቷ ሴት ጋራ የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር። 15.እንዲሁም የተገደለችዋ ምድያማዊት ሴት ከስቢ ትባላለች፤ እርሷም ከምድያማውያን ቤተ ሰብ የአንዱ ነገድ አለቃ የሆነው የሱር ልጅ ነበረች። 16.እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 17.“ምድያማውያንን እንደ ጠላት ቈጥራችሁ ፍጇቸው። 18.ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለ ሠሩባችሁ ነው።”የሉቃስ ወንጌል
ምዕራፍ 1
መግቢያ
1፥1-4 ተጓ ምብ – ሐሥ 1፥1
1.በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ነገሮች ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸውን ያህል ጽፈውት ይገኛል፤
2.ይህም ታሪክ ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ያስተላለፉልን ነው።
3.ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፤ እኔም በበኩሌ ሁሉን ከመሠረቱ በጥንቃቄ ከመረመርሁ በኋላ፣ ታሪኩን ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፤
4.ይህንም የማደርገው የተማርኸው ነገር እውነተኛ መሆኑን እንድታውቅ ነው።
የመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ አስቀድሞ ተነገረ
5.በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን፣ ከአብያ የክህነት ምድብ የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ነገድ ስትሆን፣ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ። 6.ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዐት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ 7.ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ። 8.አንድ ቀን ዘካርያስ በምድቡ ተራ፣ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ፣ 9.በሥርዐተ ክህነቱ መሠረት፣ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን በዕጣ ተመረጠ። 10.ዕጣን በሚታጠንበትም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ሆኖ ይጸልይ ነበር። 11.የጌታም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተቀኝ ቆሞ ታየው። 12.ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ። 13.መልአኩ ግን እንዲህ አለው፤ “ዘካርያስ ሆይ፤ አትፍራ፤ ጸሎትህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። 14.በርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ፤ ብዙዎችም እርሱ በመወለዱ ደስ ይላቸዋል፤ 15.በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ በእናቱም ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል። 16.ከእስራኤልም ሰዎች ብዙዎቹን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳቸዋል፤ 17.የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፣ የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ፣ ለጌታ የተገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኀይል በጌታ ፊት ይሄዳል።” 18.ዘካርያስም መልአኩን፣ “ይህን በምን ዐውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች” አለው። 19.መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን እነግርህና ይህን የምሥራች አመጣልህ ዘንድ ተልኬአለሁ፤ 20.እነሆ፤ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፣ ይህም እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም።” 21.በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ዘካርያስ ከቤተ መቅደሱ ሳይወጣ ለምን እንደ ዘገየ በመገረም ይጠባበቅ ነበር። 22.ከወጣ በኋላም ሊያናግራቸው አልቻለም፤ በምልክት ከመጥቀስ በቀር መናገር ባለመቻሉ በቤተ መቅደስ ውስጥ ራእይ እንዳየ ተገነዘቡ። 23.ዘካርያስም የአገልግሎቱ ወቅት በተፈጸመ ጊዜ ወደ ቤቱ ተመለሰ። 24.ከዚህ በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ዐምስት ወራትም ራሷን ሰወረች፤ 25.እርሷም፣ “ጌታ በምሕረቱ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ሊያስወግድልኝ ተመልክቶ በዚህ ጊዜ ይህን አድርጎልኛል” አለች።የኢየሱስ መወለድ አስቀድሞ ተነገረ
26.በስድስተኛው ወር፣ እግዚአብሔር መልአኩ ገብርኤልን በገሊላ ወደምትገኘው ናዝሬት ወደምትባል ከተማ ላከው፤ 27.የተላከውም ከዳዊት ዘር ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ነበር፤ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። 28.መልአኩም እርሷ ወዳለችበት ገብቶ፣ “እጅግ የተወደድሽ ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን፤ ጌታ ከአንቺ ጋራ ነው፤ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” አላት። 29.ማርያምም በንግግሩ እጅግ በጣም ደንግጣ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሰላምታ ይሆን?” እያለች ነገሩን ታሰላስል ጀመር፤ 30.መልአኩም እንዲህ አላት፤ “ማርያም ሆይ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ። 31.እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። 32.እርሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ 33.በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።” 34.ማርያምም መልአኩን፣ “እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው። 35.መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፤ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ የሚወለደው ቅዱሱ ሕፃን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። 36.እነሆ፤ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተ እርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ 37.ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።” 38.ማርያምም፣ “እነሆ፤ እኔ የጌታ ባሪያ ነኝ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” አለች። ከዚያም መልአኩ ተለይቷት ሄደ።ማርያም ኤልሳቤጥን ጥየቃ ሄደች
39.ማርያምም በዚያው ሰሞን በፍጥነት ተነሥታ ወደ ደጋው አገር፣ ወደ አንድ የይሁዳ ከተማ ሄደች፤ 40.ወደ ዘካርያስ ቤትም ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ አቀረበች። 41.ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ 42.ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። 43.ለመሆኑ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? 44.እነሆ፤ የሰላምታሽ ድምፅ ጆሮዬ እንደ ገባ፣ በማሕፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሏልና። 45.ጌታ ይፈጸማል ብሎ የነገራትን ያመነች እርሷ ብፅዕት ናት!”የማርያም መዝሙር
46.ማርያምም እንዲህ አለች፤“ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤ 47.መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሠኛለች፤ 48.እርሱ የባሪያውን መዋረድ ተመልክቷልና።
ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ
ምስጉን ይሉኛል፤ 49.ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅ
ነገር አድርጎልኛልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤ 50.ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ
እስከ ትውልድ ይኖራል። 51.በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቷል፤
በልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኗቸዋል፤ 52.ገዦችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፤
ትሑታንን ግን ከፍ ከፍ አድርጓቸዋል፤ 53.የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቧቸዋል፤
ሀብታሞችን ግን ባዷቸውን ሰድዷቸዋል፤ 54.ምሕረቱን በማስታወስ፣ ብላቴናውን
እስራኤልን ረድቷል፤ 55.ይህም ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፣
ለአብርሃምና ለዘሩ ያለውን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው።” 56.ማርያምም ሦስት ወር ያህል ኤልሳቤጥ ዘንድ ከቈየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች።
የመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ
57.የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች። 58.ጎረቤቶቿና ዘመዶቿም ጌታ ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰሙ፤ የደስታዋም ተካፋዮች ሆኑ። 59.በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤ 60.እናቱ ግን፣ “አይሆንም፤ ዮሐንስ መባል አለበት” አለች። 61.እነርሱም፣ “ከዘመዶችሽ በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” አሏት። 62.አባቱንም ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት። 63.እርሱም መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ለምኖ፣ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም በነገሩ ተደነቁ። 64.ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱ ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ መናገር ጀመረ። 65.ጎረቤቶቹም ሁሉ በፍርሀት ተሞሉ፤ ይህም ሁሉ ነገር በደጋማው የይሁዳ ምድር ሁሉ ተወራ። 66.ይህንም የሰሙ ሁሉ፣ “ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ያዙ፤ የጌታ እጅ በርግጥ ከርሱ ጋራ ነበርና።የዘካርያስ ትንቢት
67.የሕፃኑም አባት ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤ 68.“የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቷልና። 69.በብላቴናው በዳዊት ቤት፣
የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፤ 70.ይህም ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው፣ 71.ማዳኑም ከጠላቶቻችንና፣
ከተፃራሪዎቻችን ሁሉ እጅ ነው፤ 72.ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣
ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣ 73.ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማሰብ፣ 74.ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶ፣
ያለ ፍርሀት እንድናገለግለው፣ 75.በዘመናችንም ሁሉ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ ሊያቆመን ነው። 76.“ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፤ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤
የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት በፊቱ ትሄዳለህና፤ 77.የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤
ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣ 78.ከአምላካችንም ጥልቅ ምሕረት የተነሣ፣
የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤ 79.ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣
በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣
እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።” 80.ሕፃኑም እያደገ፣ በመንፈስም እየጠነከረ ሄደ፤ ለእስራኤልም ሕዝብ በይፋ እስከ ታየበት ቀን ድረስ በበረሓ ኖረ።